MENU

Where the world comes to study the Bible

የእግዚአብሄር የደህንነት ዕቅድ

Related Media

1 ዮሐንስ 5፥ 11 -12  እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።

ይህ ምንባብ የምነግረን እግዚአብሄር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የዘላለም ህይወት እንደሰጠን ነው። በሌላ በኩል የዘላለም ህይወት የማግኛ መንገድ የእግዚአብሄርን ልጅ በመቀበል (በማመን) መሆኑን ነው።

ለመሆኑ አንድ ሰው የእግዚአብሄርን ልጅ እንዴት ነው የሚቀበለው?

ከእግዚአብሄር የለየው የሰው ልጅ ክፋት

ኢሳ 59 2 ነገር ግን በደላችሁ ከአምላካችሁ ለይቶአችኋል፤ ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል፤ በዚህም ምክንያት አይሰማም።

ሮሜ 5 8 ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።

በሮሜ 5 8 እንደተገለፀው እግዚአብሄር የገዛ ልጁን ለሞት አሳልፎ በመስጠት ፍቅሩን አሳየን። ክርስቶስ ስለ እኛ መሞት ስለምን አስፈለገ? አዎን ቅዱሳን መጽሀፍት የምነግሩን ሰው ሁሉ ኃጢአተኛ መሆኑን ነው።ኃጢአተኛሲል ምንም ልዩነት አለመሩን ያመለክታል።

መጽሃፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል።ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል(በሮሜ 323):: ስለሆነም ኃጢአታችን ፍጹም እንከን ከሌለበት ከቅዱስ እግዚአብሄር ስለለየን፤ እግዚአብሄር ትክክለኛ ፍርድ እና ፍትሕ ለመስጠት ሲል በኃጢአተኛ ሰው ላይ የግድ ይፈርዳል።

ዕንባቆም 113 ዓይኖችህ ክፉ እንዳያዩ ንጹሐን ናቸው፥ ጠማምነትንም ትመለከት ዘንድ አትችልም፤ አታላዮችንስ ለምን ትመለከታለህ? ኃጢአተኛውስ ከእርሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጠው ስለ ምን ዝም ትላለህ?

ዋጋ ቢስ ስለሆነዉ የጽድቅ ስራችን

ምንም ያህል የሆነ የሰው ልጅ ደግነት፥ ስራ፥ ቅንነት፥ ወይም ሃይማኖታዊ ስርዓት በአምላክ ዘንድ ወይም በሰማይ ተቀባይነት የሌላቸው መሆናቸዉን ቅዱስ መጽሀፍ ያስተምረናል።

ጨዋ ሀይማኖተኛ ሰዉ እንደዚሁም ጨዋ ያልሆነ እና ሀይማኖት አልባ ሰዉ ሁሉም በተመሳሳይ መርከብ ይጓዛሉ።

ሁላቸውም የእግዚአብሄር ጽድቅ ጎሎአቸዋልና።

ሐዋሪያ ቅዱስ ጳዉሎስ ሮሜ 118 38 ጨዋና ጨዋ ስላልሆነ ሰዉ እንዲሁም ስለ ሀይማኖተኛ ሰዉ ከብራራ በኋላ ሁለቱም አይሁድም የግሪክም ሰዎች ከኃጢአት በታች መሆናቻዉን በማስታወቅ ጻድቅ ማንም የለም አንድ ስንኳ በማለት በሮም 39-10 ያስረዳል

በተጨማሪ የሚከተለዉን የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስ እንመልከት።

ኤፌ 2 8-9 ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።

ቲቶ 35-7 እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤ ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።

ሮሜ 4 1-5 1 እንግዲህ በሥጋ አባታችን የሆነ አብርሃም ምን አገኘ እንላለን? 2 አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን የሚመካበት አለውና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም። 3 መጽሐፍስ ምን አለ? አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት። 4 ለሚሠራ ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቈጠርለትም፤ 5 ነገር ግን ለማይሠራ፥ ኃጢአተኛውንም በሚያደድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።

ጽድቃችን ምንም ያክል ትልቅ ቢሆን እንደ እግዚአብሄር ሊሆን አይችልም። እግዚአብሄር ፍጹም ትክክል ነዉና። ከዚህም የተነሳ በትንቢተ ዕንባቆም 113 እግዚአብሄር ፍጹም የሆነ ቅድስና ከሌላቸዉ ጋር ህብረት ሊኖረዉ እንደማይችል ይናገራል። በእግዚአብሄር ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ልክ እንደርሱ መቀደስ አለብን። ነገር ግን ሁላችን በእግዚአብሄር ፊት ስንቆም እርቃናችን ሲሆን አጋዥ እንደሌለው ተስፋ ቢሶች እንሆናለን። ምንም ያክል ስነምግባር ቢኖረን እኛን ወደ ሰማይ አይወስደንም ወይም ዘላለማዊ ህይወት አይሰጣንም።

ታዲያ መፍሄዉ ምንድን ነዉ?

እግዚአብሄር ፍጹም ቅዱስ ብቻ ሳይሆን ቅድስናዉንም በራሳችን መንገድ ወይም በራሳችን የጽድቅ ስራ ማግኘት አንችልም። በሌላ በኩል እግዚአብሄር ፍቅር፥ ጸጋ እና ምህረት የተሞላ ፍጹም አምላክ ነዉ። ከፍቅሩ እና ፀጋ የተነሳ በተስፋ መቁረጥ ዉስጥ ካለመፍትሄ አይተወንም።

ሮሜ 58 ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።

ይህም የመጽሀፍ ቅዱስ የምስራች የወንጌል መልዕክት ነው።

እግዚአብሔር ለእኛ የሰጠዉ የገዛ ልጁን ሲሆን አምላክ ሆኖ ሳለ ሰዉ ሆነ፥ ካለኃጢአት (ነቀፋ)ኖረ፥ ለኃጢአታችን በመስቀል ላይ ነፍሱን ኣሳልፎ ሰጠን፥ መቃብሩንም ፈንቅሎ በመነሳቱ ምክንያትም የእግዚአብሔር ልጅነቱንና በእኛ ፈንታ መሞቱን አረጋገጠ።

ሮሜ 1 4 ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ሮሜ 4 24-25 ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታንችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቈጠርልን ዘንድ አለው።

2 ቆሮ 521 እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።

1 ጴጥ 318 ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥

የእግዚአብሔርን ልጅ የምንቀበለዉ(የሚናምነዉ) እንዴት ነው ?

ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለፈጸመልን ደህንነት መጽሓፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል።ልጁ ያለዉ ሕይወት አለዉ ኢየሱስ ክርስቶስንም የምንቀበለዉም (የምናምነዉም) ኢየሱስ እኛን ለማዳን ሲል ሰዉ ሆኖ መወለዱን እና ለኃጢአታችን ቤዛ ሆኖ በመስቀል ላይ የሞተልን መሆኑን በማመን ነዉ።

የዮሐንስ ወንጌል 112 ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው::

የዮሐንስ ወንጌል 3 16-18 16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። 17 ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። 18 በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።

ይህም ማለት ሁላችንም ወደ እግዚአብሄር መመለስ ያለብን በተመሳሳይ መልክ:

1. ኃጢአተኛ መሆናችንን በመገንዘብ

2. ማናቸዉም የእኛ የጽድቅ ስራ ለጽድቅ የማያበቃ መሆኑን በማስታወስ

3. ሙሉ በሙሉ የይሕወት መዳን የሚፈጸምልን በክርስቶስ ባለን በእምነት መሆኑን በመቀበል ነዉ።

ስለሆነም ለመዳን፥ ኢየሱስ ክርስቶስን የግል አዳኝ አድርጎ ለመቀበልና ለማመን ከፈለጉ፥ ኃጢአተኛ መሆንዎን በማወቅ፤ የርሱን ይቅርታ ለመቀበል እና በክርስቶስ ያለትዎን እምነት በመግለጽ በመጸለይ ነዉ።

በክርስቶስ የሚያምኑም ከሆነ ስለ አዲሱ ሕይወት እና እንዴት ከጌታ ጋር መኖር እንደምቻል መማር አለብዎ። ኤቢሲ የክርስትና ዕድገት ከተሰኘዉ ፋውንደሽን ጋር በመሆን ጥናት መጀመር እንደሚቻል እንመክሮታለን። ይህ ተከታታይ፥ ደረጃ በደረጃ የሆነ እዉነት ወደ እግዚአብሄር መሰረታዊ ቃል የሚወስድ ሲሆን በክርስቶስ ፅኑ መሰረት ያለው እምነት እንድንገነባ ይረዳናል።

 

Report Inappropriate Ad